የተለመዱ ጥያቄዎች
FAQs
FAQ
የተለመዱ ጥያቄዎች
Frequently Asked Questions
የአልፋ ፈርኒቸር ሶፋ ምርቶች በተሻለ ጥራትና አስተማማኝነት ይታወቃሉ፡፡ ዋናው የሚለየን ደንበኞቻችን ሶፋ ሲገዙን ደክመውና ጥረው ለሚከፍሉት ዋጋ ገዚዎችን መጀመሪያ የአስተማማኝ እቃ ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚሰጠን ስለምንረዳ ነው፡፡
ባለፉት 19+ አመታትም በርካታ ደንበኞችን የምናገኘው ቀድሞ የገዙን ደንበኞች ለዘመድ አዝማድና ለጓደኞቻቸው መስክርውልንና ብዙ ግዜም በአካል ይዘዋቸው መጥተው ከኛ ስለሚያስገዙ ነው፡፡
ጥራትን መጠበቅ አንድም ሚስጥር የለውም፡፡
ጥራትን ለማሻሻል ሲባል የምርት ግብዐቶችን ደረጃ መጨመርና የተሻሉ የማምረት ዘዴዎችን ስራ ላይ ማዋል ግድ ይላል፡፡
የህም ተጨማሪ ወጪ ይጠይቃል፡፡ የምቶቻችንን ጥራት ስንጨምር ወጪ ስለሚኖርው በረጅም ግዜ እንጂ በአጭር ገዜ ብዙ ጥቅም እንደማናገኝ አምነንበት በመንቀሳቀስ ታዋቂነታችንንና የገበያ ድርሻችንን ቀስ በቀሰ ባለፉት አመታት አሳድገናል፡፡
በግልፅ አነጋገር ሶፋ ለሚያቀርብላቸው ድርጅት ከሸማቾ ከፍተኛ አመኔታን ይጠይቃል፡፡ ምክኒያቱም ሶፋ ሲታይ የተሸፈነ ስለሆነና ጉዱ የሚታወቀው ከቀናት ሳይሆን ከወራት በኌላ ስለሆነ፡፡ በቀላሉ የማይለወጥና ከፍ ያለ ወጪ የሚጠይቅ መሰረታዊ የቤት አቃ ቢሆንም ከአቅራቢው ድርጅት ለሸማቾች በፅሁፍ ህጋዊ ዋስትና መስጠት በገበያው ውስጥ የበለጠ ሊለመድ ይገባዋል፡፡
የአልፋ ፈርኒቸር ሶፋ ሲገዙ በፅሁፍ የሁለት አመት ዋስትና ካርድ በእጅዎት ይሰጥዎታል፡፡
ከተለመዱና ሊያጋጥሙ ከሚችሉ ችግሮች ውስጥ ለምሳሌ ሶፋ ከገዙ በኋላ ቤትዎ ሲገለገሉበት ከአገጣጠም ጉደለት ድምፅ ፤ የሚለቅ ስፌት ፤ የላላ ወይም ጭራሽ የወለቀ አግሮች እና የተመሳሰሉ ከአመራረት ጉድለት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በዝርዘር ጠቀሶ ለእነዚህ እና ተመሳሳይ ችግሮችን በሚመለከት አልፋ ፈርኒቸርን የሶፈ መርጫዎ ሲያደርጉ በፅሁፍ የሁለት አመት ዋስትና ያገኛሉ፡፡